የጉባኤው መግለጫ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዯር የመሬት ይዞታ ማስሇቀቅና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤ በከተማው ምክር ቤት በዯንብ ቁጥር 6/2014 መሰረት የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ ጉባዔው ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፤ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሽዎች መልሰዉ የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 እና በዯንብ ቁጥር 472/2012 መሠረት ከልማት ተነሺዎች የሚነሱ ቅሬታዎችን መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥ ነው፡፡
ራዕይ እና ተልዕኮ
ተልዕኮ
በከተማ አስተዳዯሩ ሇጉባኤው የሚቀርብ ከይዞታ መነሳት ወይም ምትክ ቦታ ወይም ካሳ፤ ወይም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመሇከተ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በመመርመር፤ ቀልጣፋና ውጤታማ ውሳኔ በመስጠት የአቤቱታ አቅራቢዎችን ፍትህ የማግኘት መብት፤ በማስከበር በከተማው አስተዳዯር የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡
ራዕይ
በ2022 ዓ.ም በአገልግሎት ቅልጥፍናው፤ በውጤታማነቱና በፍትሃዊነቱ የተገልጋዮችን አመኔታ ያተረፈ የመዳኘት ስልጣን የተሰጠው አካል ሆኖ ማየት፡፡
እሴቶች
- ነፃነት፤ ገሇልተኛነትና አሇማዳላት
- ተጠያቂነት
- የአሰራር ግልፀኝነት
- ፍትሀዊነት
- የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍና
- ሁሌም ሇሇውጥ ዝግጁነት
- ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የፀዳ አገልግሎት
- ተገልጋዮችን ማክበር
የጉባኤው መ/ቤት አድራሻ:
ካዛንቺስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሕንጻ ገባ ብሎ ECA ጀርባ